አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮ ቴሌኮም አመራሮች እና ሰራተኞች አዲሱን ዓመት ምክንያት በማድረግ የበጎ አድራጎት ተግባራት ማከናወን መርሐ ግብር አካሂዷል።
ተቋሙ መርሐ ግብሩን ያካሄደው ማህበራዊ ሀላፊነቱን ለመወጣት ብሎም ከደንበኞቹ ጋር አዲስ ዓመትን ለመቀበል ነው።
በዚህም በዋናው መስሪያ ቤት ደም ልገሳ የተከናወነ ሲሆን በተጨማሪም ተቋሙ ለሙዳይ የበጎ አድራጎት ማህበር 2 ሚሊየን 625 ሺህ ብር እና የትምህርት ቁሳቁሶችን ድጋፍ አድርጓል።
የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ በወቅቱ እንዳሉት÷ መልካም ስራ ማድረግ እና መከተል ትውልድን ያሸግራል፡፡
አዲሱን ዓመት የምንቀበለው ‘ቀጣዩ አድማስ’ በሚል ሰው ተኮር እና ሰውን ማዕከል ባደረገ የሶስት ዓመት ስራቴጂ ነው በማለት ገልጸው÷ በጎ ስራ ማከናወንም የተቋሙ ስትራቴጂ አካል መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡
ኢትዮ ቴሌኮም በመላ ሀገሪቱ በርካታ ስራዎችን ከሚሰሩ በጎ አድራጎት ድርጅቶች ጋር በጋራ ለመስራት በጀት መመደቡን ጠቁመዋል፡፡
በዛሬው እለትም 960 ሺህ ደብተር ድጋፍ መደረጉን ገልፀው፤ ድጋፉ 80 ሺህ ተማሪዎችን ተጠቃሚ እንደሚደርግ ጠቁመዋል፡፡
እስካሁን ተቋሙ 3 ነጥብ 2 ሚሊየን ደብተር ድጋፍ ማድረጉንም ተናግረዋል፡፡
በፌቨን ቢሻው
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!