አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ሁለንተናዊ የተቋም ማዘመን ስራችን ተጠናክሮ ይቀጥላል አሉ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ። የተሟላ ሁለገብ አገልግሎት መስጠት የሚችለው የቆሬ ሜንተናንስና ዕድሳት ማዕከል ተመርቋል።
በዚህ ወቅት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ባስተላለፉት መልዕክት፥ የመከላከያ ሰራዊቱን በሁሉም ዘርፍ የማዘመን ስራው ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል። ከ8 ሺህ ሄክታር በላይ በሆነ ቦታ ላይ የተገነባው የቆሬ ሜንተናንስና ዕድሳት ማዕከል 12 ወርክ ሾፖች፣ የአስተዳደር ህንጻ፣ ነዳጅ ማደያንና አረንጓዴ ስፍራዎችን ያካተተ ነው። ግንባታው በተለያዩ ምክንያቶች ሲጓተት የቆየና ከሀገራዊ ለውጡ በኋላ የተለያዩ ማሻሻያዎች ተደርገውለት መከላከያንም ኢትዮጵያንም በሚመጥን ልክ መገንባቱ ተገልጿል። በጃንሜዳና በሜክሲኮ በተበታተነ መልኩ ሲሰጥ የነበረን አገልግሎት ወደ አንድ ማዕከል ያመጣው የቆሬ ሜንተናንስና ዕድሳት ማዕከል የአገልግሎት ጥራትን ያረጋገጠ መሆኑን ተመላክቷል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!