የሀገር ውስጥ ዜና

በሲዳማ ክልል የጽናት ቀን እየተከበረ ነው 

By Mikias Ayele

September 06, 2025

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሲዳማ ክልል ጳጉሜን 1 የጽናት ቀን ‘ጽኑ መሠረት፤ ብርቱ ሀገር’ በሚል መሪ ቃል እየተከበረ ይገኛል፡፡

በመርሃ ግብሩ የሲዳማ  ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ፋንታዬ ከበደ እንዳሉት÷ ዘንድሮ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ተጠናቆ በምረቃ ዋዜማ ላይ በመሆን የጽናት ቀን መከበሩ የጽናት ውጤትን በተግባር ያሳየ ነው።

በለውጡ ዓመታት ብዙ ፈተናዎች የገጠሙ ቢሆንም ፈተናዎችን በጽናት በመሻገር ዘርፈብዙ ድሎችን አስመዝግበናል ብለዋል።

እየተጠናቀቀ ያለው 2017 የጥፋት ኃይሎች የደቀኑትን ፈተናዎች በጠንካራ አመራር ሰጪነት በማለፍ እምርታዊ ድል የተመዘገበበት እንደሆነ ገልጸው÷ አሁንም በትብብር ከሰራን የማንሻገረው ችግር የለም ነው ያሉት፡፡

በመርሐ ግብሩ የሀገር መከላከያ ሰራዊት እና የፌደራል ፖሊሲ አባላት፣ የሲዳማ ክልል ፖሊስ አባላት እንዲሁም የክልሉ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡