የሀገር ውስጥ ዜና

በሀረሪ ክልል የጽናት ቀን ተከበረ

By Mikias Ayele

September 06, 2025

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሀረሪ ክልል ጳጉሜን 1 የጽናት ቀን ‘ጽኑ መሰረት፤ ብርቱ ሀገር’ በሚል መሪ ቃል በተለያዩ መርሃ ግብሮች ተከብሯል።

የክልሉ  ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ በሥነ ሥርዓቱ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት÷ ወቅቱ ለትውልድ ጠንካራ መሰረት የምንጥለበት ነው ብለዋል።

ጊዜው የብልፅግና ማማን ለመጨበጥ በጽኑ መቆማችንን የምናውጅበት ነው በማለት ገልጸው÷ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በስኬት መጠናቀቅ ለዚህ አንዱ ማሳያ እንደሆነ ተናግረዋል።

ክልሉ በ2017 በጀት ዓመት በሁሉም ዘርፎች የጽናት ማሳያ የሆኑ አበረታች ውጤት ማስመዝገቡን አንስተዋል።

በሁሉም ዘርፎች የተመዘገቡ ውጤቶች የብልፅግና ጉዞው ሁሉን አቀፍ መሆኑንና በተባበረ ክንድ የማናሳከው ነገር አለመኖሩን አሳይቷል ብለዋል።

የሚጠብቀን የከፍታ ጉዞ ጠንካራ ጽናት፣ እምርታና ማንሰራራትን የሚጠይቅ በመሆኑ የተመዘገቡ ውጤቶችን ለማስፋት በጽናት መቆም ይገባናል ሲሉ መልዕክታቸውን  አስተላልፈዋል፡፡

በተስፋዬ ኃይሉ