የሀገር ውስጥ ዜና

የዳውሮ ብሔር የዘመን መለወጫ በዓል “ቶኪ በኣ” እየተከበረ ነው

By Mikias Ayele

September 06, 2025

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የዳውሮ ብሔር የዘመን መለወጫ እና የምስጋና በዓል የሆነው “ቶኪ በኣ” በተለያዩ ሥነ ሥርዓቶች እየተከበረ ይገኛል።

‎በዓሉ አሮጌውን ዓመት በመሸኘት አዲሱን ዓመት በተስፋ የሚቀበሉበት የደስታ፣ የሰላም እና የአንድነት መገለጫ መሆኑ ተገልጿል።

እንዲሁም የተጣሉት የሚታረቁበት፣ ወዳጅ ዘመድ የሚመራረቅበት መጪው ዓመት የሰላም፣ የፍቅር፣ የጥጋብ እንዲሆን የአባቶች ምርቃት ለልጆች የሚቀርብበት ነው።

በዓሉ በዳውሮ ብሔር አባላት ዘንድ በናፍቆት ከሚጠብቁበ በዓላት መካከል አንዱ ባህላዊ እሴት በመሆኑ ተጠብቆ እና ለምቶ ለመጪው ትውልድ እንዲተላለፍ ሁሉም ባለድርሻዎች ተቀናጅተው መስራት እንዳለባቸው ተመላክቷል።