የሀገር ውስጥ ዜና

የጽናት ቀን በጋምቤላ ከተማ ተከበረ

By Mikias Ayele

September 06, 2025

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በጋምቤላ ክልል ጋምቤላ ከተማ ጳጉሜ 1 የጽናት ቀን ‘ጽኑ መሠረት፤ ብርቱ ሀገር’ በሚል መሪ ቃል በተለያዩ  መርሃ ግብሮች ተከብሯል።

በሥነ ሥርዓቱ ላይ የተለያዩ ወታደራዊ ትርዒቶች የቀረቡ ሲሆን፤ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ወይዘሮ አለሚቱ ኡሞድን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።

እንዲሁም የሀገር መከላከያ ሰራዊትና የፌዴራል ፖሊስ አመራሮች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል፡፡