የሀገር ውስጥ ዜና

በሶማሌ ክልል የጽናት ቀን ተከበረ

By Abiy Getahun

September 06, 2025

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሶማሌ ክልል ጳጉሜን 1 የጽናት ቀን ‘ጽኑ መሰረት፤ ብርቱ ሀገር’ በሚል መሪ ቃል በጅግጅጋ ከተማ ተከብሯል።

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጽሕፈት ቤት ሃላፊ ሁሴን ቃስን (ዶ/ር) በሥነ ሥርዓቱ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት÷ በፅናትና በትብብር ለሰላም ግንባታና ልማት ጠንክረን እንሰራለን ብለዋል፡፡

ለሀገራችን መጽናትና ሰላም መስፈን መስዋዕትነት የከፈሉ ጀግኖችን በማስታወስ የኢትዮጵያን ልማትና ዕድገት ማስቀጠል ይኖርብናል ነው ያሉት፡፡

ጸንተን በጋራ በመተባበር ለክልላችን ብሎም ለሀገራችን ሰላም ግንባታ፣ ልማትና ዕድገት መትጋት አለብን ሲሉም አስገንዝበዋል፡፡

በመርሐ ግብሩ የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ የመከላከያ ሰራዊትና የፌዴራል ፖሊስ አመራሮችን ጨምሮ ሌሎችም የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል፡፡

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!