አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጳጉሜን 1 የጽናት ቀን ‘ጽኑ መሠረት፤ ብርቱ ሀገር’ በሚል መሪ ቃል በአሶሳ ከተማ በተለያዩ መርሃ ግብሮች ተከብሯል።
የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ጌታሁን አብዲሳ በሥነ ሥርዓቱ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፤ በኢትዮጵያውያን የተባበረ ጥረት የተገነባው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በጽናት ለስኬት የበቃንበት ነው ብለዋል፡፡
በለውጡ ዓመታት የኢትዮጵያውያን የጽናት ማሳያዎችና በትብብር ተጨባጭ ውጤት የተመዘገበባቸው የስኬት ተምሳሌቶች መኖራቸውን ገልጸው፤ በቀጣይም ፈተናዎችን ወደ ዕድል በመቀየር እና በጽናት በመሻገር ልማት በጋራ ማስቀጠል እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡
በዕለቱ በማርቺንግ ባንድ የታጀበ የእግር ጉዞ የተደረገ ሲሆን የኢትዮጵያን የጽናት ማሳያዎችና የከፍታ ጉዞ የሚያወሱ የስነ ጽሁፍ ስራዎች መቅረባቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
በመርሃ ግብሩ ላይ የመከላከያ ከፍተኛ አመራሮችና አባላት፣ የክልሉ አመራሮችና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተወካዮች ተገኝተዋል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!