የሀገር ውስጥ ዜና

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ አዲሱን የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ ቢሮ መርቀው ከፈቱ

By Abiy Getahun

September 06, 2025

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የመከላከያ መሃንዲስ ዋና መምሪያ በኮዬ ፈጬ ያስገነባውን አዲሱን የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ ቢሮ መርቀው ከፍተዋል፡፡

ጠቅላይ መምሪያውን በባለቤትነት ያሰራው የመከላከያ መሃንዲስ ዋና መምሪያ ሲሆን ግንባታውን ያከናወነው ደግሞ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬችን መሆኑ ተመላክቷል።

ጠቅላይ መምሪያው በውስጡ ዘመናዊ የስፖርት ማዘውተሪያ፣ የነዳጅ ዲፖ፣ መሰብሰቢያ አዳራሽ፣ የጋራዥ ወርክ ሾፕ እና መሰል ግንባታዎችን አካትቷል።

የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ ደረጃውን የጠበቀ የውስጥ ለውስጥ አስፓልት መንገድ ሥራንም ያካተተ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

በሳራ ስዩም

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!