አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአንጎላ ፕሬዚዳንት ጆኣኦ ሎሬንቾ በሁለተኛው የአፍሪካ ካሪቢያን ማህበረሰብ ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል።
ፕሬዝዳንቱ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) ተቀብለዋቸዋል፡፡
በተመሳሳይ የሀገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ቴቴ አንቶኒዮ ለጉባኤው አዲስ አበባ የገቡ ሲሆን፤ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ ተቀብለዋቸዋል፡፡
ሁለተኛው የአፍሪካ ካሪቢያን ማህበረሰብ ጉባዔ “ለአፍሪካውያንና ዘርዓ አፍሪካውያን የማካካሻ ፍትህን ለመሻት አህጉር ተሻጋሪ አጋርነት” በሚል መሪ ሃሳብ ዛሬ በአዲስ አበባ ይካሄዳል።
ጉባዔው የአፍሪካና ካሪቢያን ሀገራት በደቡብ ደቡብ የትብብር መንፈስ ግንኙነታቸውን ለማጎልበት፣ አፍሪካ ከካረቢያን ሀገራት ጋር ያላትን ግንኙነት ወደ ጠንካራ የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ እና ትብብር ለማሳደግ ያስችላል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ጉባዔው በዓለም የፋይናንስ ስርዓት፣ በቱሪዝም፣ በሰው ሰራሽ አስተውሎት ላይ ይመክራል።
በአሸናፊ ሽብሩ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.) Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook WMCC TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!