አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የግብርና ሚኒስትር አዲሱ አረጋ የቡና ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የተሰጠው ትኩረት የላቀ ውጤት እያመጣ ነው አሉ።
ሚኒስትሩ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ጉጂ ዞን ገላና ወረዳ በመገኘት በቀርጫንሼ ግሩፕ የለማውን የቡና ተክል ተመልክተዋል።
ከጉብኝታቸው በኋላ በሰጡት ማብራሪያ ለቡና ልማት በመንግስት ልዩ ትኩረት መሰጠቱን ገልጸው፤ ይህም የቡና ምርትን በማሳደግ ረገው የላቀ ውጤት እያመጣ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
በቀርጫንሼ ግሩፕ የቡና ልማት የውጤቱ ማሳያ መሆኑን አንስተው፤ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዘው ይህ የቡና ልማት የጥራትና ምርታማነት ጥሩ ተሞክሮ የታየበት ነው ብለዋል።
ተመሳሳይ ልማት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ማረጋገጣቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
የቀርጫንሼ ግሩፕ ሥራ አስኬያጅ እስራኤል ደገፋ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ በመንግስት እየተደረገ ያለው ድጋፍ ለውጤታማነት እንዳበቃቸው እና በጥራትና ምርታማነት ላይ ስኬት መመዝገቡን ተናግረዋል።
በገላና ወረዳ ቡናን ከጥላ ዛፍ ውጭ የማልማት ተግባር ከ750 ሄክታር በላይ በሆነ መሬት ላይ መከናወኑንም ጠቁመዋል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!