ስፓርት

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑክ ሽኝት ተደረገለት

By Abiy Getahun

September 06, 2025

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በጃፓን ቶኪዮ በሚካሄደው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ ለሚሳተፈው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑካን ቡድን ሽኝት ተደረገለት፡፡

ኢትዮጵያ በሻምፒዮናው የርምጃ ውድድርን ጨምሮ ከ800 ሜትር እስከ ማራቶን ባሉት ርቀቶች የምትካፈል ይሆናል፡፡

በሽኝት መርሀ ግብሩ ላይ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ አምባሳደሮች፣ የፌዴሬሽኑ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላትና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

20ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ከመስከረም 3 ቀን እስከ መስከረም 11 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ በጃፓን ቶኪዮ ይካሄዳል።