አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የጋምቢያ ምክትል ፕሬዚዳንት ሞሃመድ ጃሎ እና የጅቡቲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ሁሴን አብዱልቃድር አዲስ አበባ ገብተዋል።
የሰላም ሚኒስትር መሀመድ እድሪስ በቦሌ ዓለም አቀፍ የአውሮፕላን ማረፊያ ተገኝተው ለልዑካኑ አቀባበል አድርገዋል፡፡
ልዑካኑ በኢትዮጵያ ቆይታቸው በአፍሪካ-ካረቢያን ማህበረሰብ ጉባኤ እና በአፍሪካ አየር ንብረት ጉባኤ ላይ ይሳተፋሉ፡፡
በተመሳሳይ የአፍሬክሲም ባንክ ፕሬዚዳንት ቤኔዲክት ኦራማህ በአፍሪካ-ካረቢያን ማህበረሰብ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!