አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያውያን ረጅም ዘመናትን በተራመደ የታሪክ ዐሻራ የተሠራን የኅብር ሸማ ነን አሉ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)፡፡
የኅብር ቀን “ብዝኃነት የኢትዮጵያ ጌጥ” በሚል መሪ ሀሳብ በዛሬው ዕለት እየተከበረ ይገኛል፡፡
ርዕሰ መስተዳድሩ ዕለቱን አስመልክተው ባስተላለፉት መልዕክት እንዳሉት፥ ብዝሃነት የኢትዮጵያ ጌጥ፣ ውበትና የጥንካሬያችን ምንጭ ነው፡፡
እኛ ኢትዮጵያውያን በዝንቅ ቀለማት የደመቅን፣ በብዝኃነት ያጌጥን፣ በጋራ መስተጋብሮች የተጋመድን፣ ረጅም ዘመናትን በተራመደ የታሪክ ዐሻራ የተሠራን የኅብር ሸማ ነን ብለዋል።
ኢትዮጵያውያን ለወል እሴትና ለወል እውነት ማፅኛ መሠረት የሆኑ ዘመን ተሻጋሪ መስተጋብሮች እንዳሏቸው ጠቅሰው፥ ለሕብረ ብሔራዊ አንድነት ማበብና ለጋራ ትርክት ግንባታ መጠናከር እየተጋን እንገኛለን ነው ያሉት፡፡
የኅብር ቀንን ስናከብር ብዝኃነትን ያከበረ ሕብረ ብሔራዊ አንድነትን ለማጎልበት፣ የወንድማማችነትእሴቶችን ለማጠናከር፣ በጋራ ሕልም የጋራ ሀገራችንን ወደ ተሻለ ምዕራፍ ለማሻገር የበኩላችንን ለማበርከት ቃላችንን እያደስን መሆን እንዳለበት አስገንዝበዋል፡፡
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!