የሀገር ውስጥ ዜና

ጉባኤዎቹ በሰላም እንዲካሄዱ አስፈላጊው ዝግጅት ተደርጓል – የፌደራል ፖሊስ

By Yonas Getnet

September 07, 2025

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአዲስ አበባ ለሚካሄዱት 2ኛው የአፍሪካ አየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ እና የአፍሪካ-ካሪቢያን የመሪዎች ጉባኤ አስፈላጊው ዝግጅት ተደርጓል አለ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ፡፡

ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ጋር በመተባበር ያዘጋጀችው 2ኛው የአፍሪካ አየር ንብረት ለውጥ ጉባኤን ጨምሮ የአፍሪካ-ካሪቢያን መሪዎች ጉባኤ እና በቀጣይም የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ በአዲስ አበባ ከተማ እንደሚካሄዱ ይታወቃል።

በመሆኑም የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከሌሎች የፀጥታና ደኅንነት ኃይሎች ጋር በመቀናጀት ጉባኤዎቹ ያለምን የፀጥታ ችግር በሰላም እንዲካሄዱ ለማድረግ ከጉባኤዎቹ ቅድመ ዝግጅት ምዕራፍ እስከ ፊፃሜ ድረስ በቴክኖሎጂ የታገዘ የሰው ኃይል ስምሪት አድርጓል።

ከዚህ በተጨማሪ የትራፊክ ፍሰቱን ለማሳለጥ በርካታ የትራፊክ ፖሊሶችም ስምሪት ወስደው የትራፊክ ቁጥጥርና ክትትል እንደሚያደርጉ እየገለፀ መንገዶች እንዳይጨናነቁ ኅብረተሰቡም የድርሻውን እንዲወጣ ተጠይቋል።

ኅብረተሰቡ እስካሁን እያሳየ ላለው ድጋፍ ምስጋውን እያቀረበ በቀጣይ ለሚኖሩ አጠቃላይ የፀጥታና የትራፊክ ደንብ ለማስከበር በሚደረገው እንቅስቃሴ ውስጥ ትብብሩን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርቧል።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!