የሀገር ውስጥ ዜና

የኅብር ቀን በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በተለያዩ ዝግጅቶች ተከበረ

By Yonas Getnet

September 07, 2025

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኅብር ቀን ‎”ብዝኃነት የኢትዮጵያ ጌጥ” በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በተለያዩ ዝግጅቶች ተከብሯል።

በበዓሉ ላይ ኅብር፣ አንድነት፣ የጋራ እሴቶችን የሚያንፀባርቁ የተለያዩ ኩነቶች የቀረቡ ሲሆን፥ ዕለቱን በማስመልከት የማዕድ ማጋራትና የቁሳቁስ ድጋፍ ተደርጓል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴዔታ አምባሳደር ብርሃኑ ጸጋዬ ባስተላለፉት መልዕክት፥ ኢትዮጵያውያን ያጋጠሙንን ውስጣዊና ውጫዊ ፈተናዎች በህብር የመከትን ጠንካራ የአብሮነት እሴት ያለን የጥቁር ህዝቦች የኩራት ምንጭ የሆነ አኩሪ ገድልን በጋራ የፃፍን ህዝቦች ነን።

የተቋሙ ሰራተኞችና አመራሮችን እንዲሁም በውጭ የሚገኙ ሚሲዮኖችን በማስተባበር ተቋሙ ድጋፍና እንክብካቤ ለሚያደርግላቸው 33 ታዳጊ ህፃናት የገንዘብ፣ የምግብ ግብዓቶች፣ የአልባሳትና የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ መደረጉንም አመልክተዋል።

በተጨማሪም በተቋሙ ዝቅተኛ ደሞዝ ተከፋይ ለሆኑ ሰራተኞች አዲሱን ዓመት በማስመልከት የማዕድ ማጋራት በማድረግ ዕለቱን አክብረናል ብለዋል።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!