የሀገር ውስጥ ዜና

የእመርታ ቀን የልማት እመርታዎችን እየደመርን ወደ አዲስ ምዕራፍ ማሸጋገር የምንጀምርበት ነው – አቶ ኦርዲን በድሪ

By Yonas Getnet

September 08, 2025

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 3፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የእመርታ ቀን የልማት ጉዞ እመርታዎችን እየደመርን ወደ አዲስ ምዕራፍ ማሸጋገር የምንጀምርበት ነው አሉ የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ፡፡

የእመርታ ቀን “እመርታ ለዘላቂ ከፍታ” በሚል መሪ ቃል በዛሬው ዕለት እየተከበረ ይገኛል፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ ዕለቱን አስመልክተው ባስተላለፉት መልዕክት፥ ይህ ቀን በሁሉም የብልጽግና ዘርፎች ክልላችንና ሀገራችንን ወደላቀ ዘላቂ እመርታ ለማድረስ የገባነውን ቃል ኪዳን የምናድስበት ነው ብለዋል።

የእመርታ ቀን በሀረሪ ክልልም ሆነ በሀገራችን አጠቃላይ የልማት ጉዞ እመርታዎችን በመደመር ወደ አዲስ ቀጣይ ምዕራፍ ማሸጋገር የሚጀመርበት ዕለት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በመተጋገዝና አንድነታችንን በማጠናከር “እመርታ ለዘላቂ ከፍታ” የሚለውን መሪ ቃል እውን ማድረግ እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

ሁሉም በተሰማራበት የሙያና የኃላፊነት መስክ ዘላቂነት ያለው ፈጣን እመርታ ለማረጋገጥና ለቀጣይ ትውልድ የበለፀገ ክልልና ሀገር ለማስረከብ በላቀ ትጋት፣ በጋለ መነሳሳትና በማያቋርጥ ጥረት እንዲንቀሳቀስ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!