አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 3፣ 2017 (ኤፍ ኤምሲ) የባሕር ዳርን የኮሪደር ልማት ከጣና ውበት ጋር በማገናኘት ከተማዋን ለኑሮ ምቹና ለቱሪዝም ተመራጭ ለማድረግ እየተሰራ ነው፡፡
ጳጉሜን 3 የእመርታ ቀን በባሕር ዳር የመንግስት የሥራ ሃላፊዎችና የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች በተገኙበት ተከብሯል፡፡
የባሕርዳር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ም/ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ በሁሉም መስኮች ምርታማነትን የማሳደግና ዘመናዊ ከተማ የመገንባት ሥራ ተጠናክሮ ቀጥሏል።
የባሕር ዳርን የኮሪደር ልማት ከጣና ውበት ጋር በማገናኘት ከተማዋን ለኑሮ ምቹና ለቱሪዝም ተመራጭ ማድረግ እየተቻለ መሆኑን ጠቁመው÷ ሥራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።
በኮሪደር ልማቱ የጣናን ውበት በመግለጥ፣ የዓባይ ድልድይና የ22 ኪሎ ሜትር የአስፓልት መንገዶችን በጥራት በማከናወን የተሰናሰሉ የልማት ሥራዎችን ማሳካት መቻሉንም ተናግረዋል።