የሀገር ውስጥ ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በአፍሪካ ተፈጥሮን መሠረት ባደረገ የኃይል ሽግግር ላይ ውይይት አካሄዱ

By Yonas Getnet

September 08, 2025

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 3፣ 2017 (ኤፍ ኤምሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአፍሪካ ተፈጥሮን መሠረት ያደረገ የኃይል ሽግግርን አስመልክቶ የምሳ ላይ የውይይት መርሐ ግብር አካሂደዋል።

ውይይቱ ለለውጥ በማይበገር እና አካታች የኃይል ምንጭ ሥርዓት ማዕከል ውስጥ የኃይል አቅርቦትን የማሳለጥ ሥራ ላይ ያተኮረ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡

የምክክር መርሐ ግብሩ የሁለተኛው የአፍሪካ የአየር ንብረት ጉባዔ አካል መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!