የሀገር ውስጥ ዜና

በክልሉ ለ853 የሕግ ታራሚዎች ይቅርታ ተደረገ

By Yonas Getnet

September 10, 2025

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 5፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ የይቅርታ አዋጁን መስፈርት ላሟሉ 853 የሕግ ታራሚዎች ይቅርታ አድርጓል።

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ እንዳሉት፤ መልካም ሥነ-ምግባር ያሳዩ እና የይቅርታ መስፈርትን ማሟላታቸው በክልሉ የይቅርታ ቦርድ ተጣርቶ ለቀረቡ እና ሌሎች ተጨማሪ መስፈርቶችን ላሟሉ የሕግ ታራሚዎች ይቅርታ ተደርጓል።

ይቅርታ የተደረገላቸው የህግ ታራሚዎች ይቅርታ በማያስከለክሉ ወንጀሎች ተሳትፈው በማረሚያ ቤት የቆዩ፣ በጤና ችግር፣ በዕድሜ መግፋትና ከሕጻናት ጋር አብረዉ የታሰሩ እንዲሁም ከተፈረደባቸው ሲሶ እና ከግማሽ በላይ የፍርድ ጊዜያቸውን ያጠናቀቁ ናቸው ብለዋል።

ይቅርታ ከተደረገላቸው መካከል 54 ሴቶች ሲሆኑ 799 ደግሞ ወንዶች መሆናቸውንም አመልክተዋል።

የይቅርታው ተጠቃሚዎች የይቅርታን እሴት ተላብሰው ሰላም ወዳድ፣ ለሕግ ተገዥና አምራች ዜጋ በመሆን የበደሉትን ህብረተሰብ በማገልግል በልማት ሊክሱ እንደሚገባ ማሳሰባቸውን የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ጽ/ቤት ገልጿል።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!