የሀገር ውስጥ ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ

By Mikias Ayele

September 10, 2025

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 5፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ማያርዲት ጋር ተወያይተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕከት÷ ዛሬ ጠዋት የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኬር ማያርዲትን በጽሕፈት ቤታችን ተቀብዬ በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ተወያይተናል ብለዋል።

በውይይቱ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ትብብር ለማጠናከርና የጋራ ቅድሚያ የሚሰጣቸው ጉዳዮችን በተመለከት ምክክር ማድረጋቸውን ገልጸዋል፡፡