አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 5፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ለ2018 አዲስ ዓመት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ፡፡
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው፥ ያለፈው ዓመት የግድባችንን ፍፃሜ አብስሮ በሁሉም ያቀድናቸው ተግባራት የነበረን አፈጻጸም መልካም ሆኖ አልፏል ብለዋል።
የሚገባንን ያህል ባይሆንም የምንችለውን ያህል ሠርተንበታል፥ ታላላቅ ስኬቶችን አግኝተንበታል ነው ያሉት።
ከዛሬ ነገ ይበልጣል፣ ያልተነካ ብዙ ሀብት አለው ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ ከትናንት የተማርነው ልምድ፣ ያካበትነው ወረትና ታላላቅ ዕቅዶች ከፊታችን አሉ ሲሉ አመልክተዋል፡፡
እነዚህ ዕቅዶች ሲፈፀሙ የትናንትናዋን ኢትዮጵያ ከነገዋ የሚለዩና የኢትዮጵያን ማንሠራራት መሠረት አስይዘው ብልጽግናን ይበልጥ የሚያረጋግጡ እንደሚሆኑ ጠቁመዋል፡፡
ኢትዮጵያን የምንወድ ሁሉ ለኢትዮጵያ የማንሰራራት ዘመን በጋራ በመትጋት ታሪክ እንስራ ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል፡፡