አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 5፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ከጳጉሜን 3 እስከ 5 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሲካሄድ የቆየው ሁለተኛው የአፍሪካ አየር ንብረት ጉባኤ ተጠናቅቋል።
በማጠናቀቂያ መርሃ ግብሩ ላይ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ እንዳሉት፤ በጉባኤው የአየር ንብረት ጉዳይ ላይ ከመወያየት ባሻገር የጋራ ነገ የወሰነበት ነው።
አፍሪካ የሌሎችን የድጋፍ እጅ የምትጠብቅ ሆና የተቀረጸች ሳትሆን የመፍትሄም አካል ናት ብለዋል።
አፍሪካ በውስጧ የያዘችውን የአረንጓዴ ኃይል ክምችት መጠበቅ እንዳለባት አስገንዝበዋል።
ለዚህ ደግሞ ደንን ማልማት እና የውሃ ሃብቶቻችንን ዳግም እንዲያገግሙ ማድረግ እና የመሬት መራቆትንም መከላከል አለብን ነው ያሉት።
የአፍሪካን ነገ አፍሪካውያን ራሳቸው መገንባት እንዳለባቸው ጠቅሰው፤ ለአብነትም በዜጎች ሃብት እና እውቀት የተገነባውን ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን አንስተዋል።
በይስማው አደራው