አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 5፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ከችልድረን ኢንቨስትመንት ፈንድ ፋውንዴሽን (ሲአይኤፍኤፍ) መስራች እና የቦርድ ሊቀመንበር ሰር ክሪስቶፈር ሆን ጋር ተወያይተዋል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ ሰር ክሪስቶፈር ሆን ኢትዮጵያ በምግብ እና ሥርዓተ ምግብ ስትራቴጂ፣ በሰቆጣ ቃል ኪዳን፣ በግሪን ኢነርጂ፣ በእናቶች፣ በሴቶች እና በህጻናት ጤና ላይ እየሰራች ያለዉ ስራ የሚበረታታ መሆኑን ነግረውኛል ብለዋል።
በእነዚህ ጉዳዮች ላይ ሲአይኤፍኤፍ ድጋፉን እንደሚያጠናክር ሊቀመንበሩ ቃል መግባታቸውን ጠቅሰው፤ ድርጅቱ ሕዝብን ተጠቃሚ የሚያደርጉ በተለይ በንጹህ ውሃ አቅርቦትና በሴቶች የስራ እድል ፈጠራ ላይ የመስራት ፍላጎት እንዳለው ገልጸዋል ነው ያሉት፡፡
በተጨማሪም ሊቀ መንበሩ የኢትዮጵያ ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም በዕጅጉ እንዳስደነቃቸው ተናግረዋል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!