አዲስ አበባ፣ መስከረም 2፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) እምቅ ሃብቶችን በማልማትና የጋራ እሴቶችን በማጎልበት የሕዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተጠናከረ ጥረት ይደረጋል አሉ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ፡፡
አቶ ጥላሁን በክልሉ ባለፉት የለውጥ ዓመታት በርካታ ስኬቶች መመዝገባቸውን እና በቀጣይ ለላቀ ውጤት ሁለንተናዊ ዝግጅት መደረጉን ተናግረዋል፡፡
በየደረጃው ያለው አመራር በቁርጠኝነት ለውጤት ለመብቃት መስራት እንዳለበት ጠቁመው÷ የሕዝቡ የልማት ተሳትፎም ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ አመልክተዋል።
በመሆኑም በክልሉ ያሉ እምቅ ሃብቶችን በማልማትና የጋራ እሴቶችን በማጎልበት የሕዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተጠናከረ ጥረት ይደረጋል ነው ያሉት፡፡
የገቢ አቅምን ማሳደግ፣ ከተሞችን ማዘመንና ለነዋሪዎች ምቹ ማድረግ፣ የሥራ እድል ፈጠራ እና ኢንቨስትመንትን የማስፋፋስት ሥራ ትኩረት እንደተሰጠውም አንስተዋል።
በክልሉ ያለውን እምቅ ሃብት በማልማት፣ የቡና እና የአትክልትና ፍራፍሬ ልማትን በማጠናከር እንዲሁም የግብርና ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ ከተረጅነት የመውጣት ጥረት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ጠቅሰዋል፡፡
የቱሪዝም መዳረሻዎችንና የማዕድን ሃብቶችን በማልማት እንዲሁም በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚታዩ ማነቆዎችን በመፍታት በክልሉ ሁለንተናዊ ልማትን ለማሳካት ተዘጋጅተናል ሲሉም አረጋግጠዋል።
በ2018 በትጋት፣ ጽናትና ብቃት በመስራት የኢትዮጵያን የማንሠራራት ጉዞ ለማሳካት በሚደረገው ጥረት ክልሉ ሁነኛ አቅም ሆኖ ለመገኘት የሚያስችል ቁመና ላይ ይገኛል ማለታቸውንም ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!