አዲስ አበባ፣ መስከረም 3፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ4ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ኒውካስል፣ ቦርንማውዝ እና ፉልሃም ተጋጣሚዎቻቸውን አሸንፈዋል፡፡
ቀን 11 ሰዓት ላይ በተደረገው ጨዋታ ኒውካስል ዎልቭስን 1 ለ 0፣ ቦርንማውዝ ብራይተንን 2 ለ 1 እንዲሁም ፉልሃም ሊድስ ዩናይትድን 1 ለ 0 አሸንፈዋል፡፡
ክሪስታል ፓላስ ከሰንደርላንድ እንዲሁም ኤቨርተን ከአስቶንቪላ ጋር ያደረጉት ጨዋታ ያለምንም ግብ በአቻ ውጤት ተጠናቅቋል፡፡