የሀገር ውስጥ ዜና

ቶተንሃም ዌስትሃም ዩናይትድን 3 ለ 0 አሸነፈ

By Mikias Ayele

September 13, 2025

አዲስ አበባ፣ መስከረም 4፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አራተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ቶተንሃም ዌስትሃም ዩናይትድን 3 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡

ምሽት 1 ሰዓት ከ30 ላይ በዌስትሃም ሜዳ በተደረገ ጨዋታ ፓፔ ሳር፣ ሉካስ ቤርጋቫል እና ሚኪ ቫን ዴ ቬን የቶተንሃምን የድል ጎሎች አስቆጥረዋል፡፡

በጨዋታው የዌስትሃሙ ተከላካይ ቶማስ ሶቼክ ባሳየው ያልተገባ ባህሪ በቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል፡፡

ቀደም ሲል በተደረጉ ጨዋታዎች አርሰናል፣ ኒውካስል፣ ቦርንማውዝ እና ፉልሃም ተጋጣሚዎቻቸውን ሲያሸንፉ ክሪስታል ፓላስ ከሰንደርላንድ እንዲሁም ኤቨርተን ከአስቶንቪላ ጋር ያለምንም ግብ በአቻ ውጤት ተለያይተዋል።