አዲስ አበባ፣ መስከረም 4፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ፈተና 1 ሺህ 249 ትምህርት ቤቶች ምንም ተማሪ ማሳለፍ አልቻሉም አሉ።
የዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ውጤትን በተመለከተ ማብራሪያ የሰጡት የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) እንዳሉት÷ 1 ሺህ 249 ትምህርት ቤቶች ምንም ተማሪ ማሳለፍ አልቻሉም።
በፈተናው ከፍተኛ ውጤት ማዝመዝገብ የቻሉ ተማሪዎች በተፈጥሮ ሳይንስ የትምህርት መስክ ከ600ው ከዶዶላ ኢፋ ቦሩ ትምህርት ቤት 591 እንዲሁም ከብስራተ ገብርኤል ትምህርት ቤት 579 ውጤት መመዝገቡን ጠቁመዋል።
በማሕበራዊ ሳይንስ የትምህርት ዘርፍ ደግሞ ከአጠቃላይ ከ600ው 562 እና 548 ውጤት መመዝገቡን ተናግረዋል።
በዘመን በየነ