አዲስ አበባ፣ መስከረም 4፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የዘንድሮ ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት እስከ ነገ ድረስ ይፋ ይደረጋል አለ የትምህርት ሚኒስቴር።
የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤትን በተመለከተ በሰጡት ማብራሪያ ነው ይህንን የገለጹት።
በዚህም ውጤቱ እስከ ነገ ቀን 6፡00 ድረስ እንደሚለቀቅ ተናግረዋል።
በአጠቃላይ 585 ሺህ 882 ተማሪዎች በወሰዱት ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል ፈተና በኬሚስትሪ የትምህርት ዓይነት ከፍተኛ ውጤት መመዝገቡን እና በአፕቲትዩድ ደግሞ ዝቅተኛው ውጤት መመዝገቡን አብራርተዋል።
ለትምህርት ቤቶች ሲደረግ የነበረው ድጋፍ፣ ለመምህራን የተሰጠው ስልጠና፣ የተማሪዎች እና የወላጆች ጥረት ለውጤቱ መሻሻል ትልቅ አስተዋጽኦ አበርክቷልም ነው ያሉት።
በመሳፍንት እያዩ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!