አዲስ አበባ፣ መስከረም 4፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኪን-ኢትዮጵያ ሙዚቃንና ባህልን ከማስተዋወቅ ባለፈ የኢትዮጵያ እና ሩሲያን ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከርና ለመገንባት የሚያግዝ ነው አለ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር።
በሚኒስቴሩ አዘጋጅነት እና በሻኩራ ፕሮዳክሽን አስተባባሪነት በተለያዩ የዓለም ሀገራት የኢትዮጵያን ባህልና ጥበብ እያስተዋወቀ ያለው ኪን-ኢትዮጵያ በሩስያ ሁለተኛ መድረኩን በሞስኮ እያካሄደ ይገኛል።
በመድረኩ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ ነፊሳ አልማህዲ ኢትዮጵያ እና ሩስያ ጥልቅና ታሪካዊ ዘመንን የተሻገረ ግንኙነት ያላቸው ሀገራት መሆናቸውን አንስተው÷ ይህ ትብብር በባህል ዲፕሎማሲና በምንጋራቸው እሴቶች እየተጠናከረ መምጣቱን ተናግረዋል።
ኪን-ኢትዮጵያ ሙዚቃና ባህልን ከማስተዋወቅ ባለፈ የሁለቱ ሀገራትን ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር እና ለመገንባት እንዲሁም መከባበርን የሚያሳይ እንደሆነ ጠቁመዋል።
መድረክ ላይ የሚቀርበውም ታሪክ እና የጥበብ ውበት የኢትዮጵያውያን ባህልና ማንነት የሚገልፅ እንደሆነ ጠቅሰው÷ ኪን-ኢትዮጵያ ወደ ፊት ለሚኖረን ትብብር የአንድነታችን ምልክት፣ እንቁ ባህል እና ተስፋ ያለው ርዕይ ነው ማለታቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!