አዲስ አበባ፣ መስከረም 4፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ብሔራዊ ድሉን ላከበረውና ብሔራዊ ጀግኖቹን ላመሰገነው የከተማዋ ነዋሪ ምስጋና አቅርበዋል።
ከንቲባዋ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የኢትዮጵያ የመቻል ማሳያ፣ የአይቀሬው ብልፅግናችን ማረጋገጫ ብሔራዊ ምልክት ነው ብለዋል።
በከፍተኛ የሀገር ፍቅር ስሜትና ድል አድራጊነት ወደ አደባባይ በመትመም ደስታውን ለገለጸው ብሔራዊ ድሉን ላከበረው እና ብሔራዊ ጀግኖቹን ላመሰገነው የአዲስ አበባ ነዋሪ በሙሉ ምስጋናዬን አቀርባለውም ነው ያሉት።
የመዲናዋ ነዋሪ የሌሊት ቁር እና ከባድ ዶፍ ዝናብ ሳይበግረው የዘመናት የትውልዶች ትግል ዉጤት የሆነውን ድል በጋራ አክብሯል ሲሉም አብራርተዋል።
ለዚህ ድል ከነበራችሁ ደጀንነት አንፃር ይገባቹሃል ያሉት ከንቲባዋ÷ ይህ ድል የኢትዮጵያ የመቻል ማሳያ፣ የአይቀሬው ብልፅግናችን ማረጋገጫ ብሔራዊ ምልክት ነው ማለታቸውን የከተማ አስተዳደሩ ኮሙኒኬሽን ለፋና ዲጂታል ገልጿል።
የከተማችን ነዋሪዎች ከመቀነቱ ፈቶ፣ ካለው ቆርሶ፣ የኑዛዜው አካል አድርጎ፣ በብዙ ዓለም አቀፍ ጫና ውስጥ በደምና አጥንት መስዋትነት በመገንባት ለፍፃሜ እንዲበቃ ያደረጉትን የሕዳሴ ግድብ ድል በታላቅ ድምቀት አክብሯል ሲሉም ነው የገለጹት።
በመርሐ ግብሩ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ፣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና የዲፕሎማሲው ማህበረሰብ መገኘታቸውንም አውስተዋል።
በዮናስ ጌትነት
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!