አዲስ አበባ፣ መስከረም 5፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ባለጉዳዮች ባሉበት ሆነው መገልገል የሚያስችላቸው የዲጅታል አሰራር በተያዘው ወር በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ይጀመራል።
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ኃላፊ ዳኛ አበበ ሰለሞን ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን እንዳሉት፤ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር በፌዴራል ፍርድ ቤቶች መሰረተ ልማት ተዘርግቷል።
አጠቃላይ የፍርድ ቤት አገልግሎቱን በዲጅታል መስጠት የሚያስችል መተግበሪያ እየለማ መሆኑን ገልጸው፤ ወደ ዲጂታል አሰራር ለመሸጋገር ‘የኤሌክትሮኒክ አቤቱታ አቀራረብ እና ሙግት’ መመሪያ ጸድቋል ብለዋል።
መመሪያው ባለጉዳዮች ባሉበት ሆነው የኤሌክትሮኒክስ አቤቱታ ለማቅረብ፣ መልስ እንዲሰጥ ከፍርድ ቤቶች ወደ ባለጉዳይ መጥሪያ ለማድረስ እንደሚያስችል ጠቅሰው፤ ባለጉዳዮች የዳኝነት ሂደቱን ባሉበት ሆነው እንዲከታተሉ የሚያስችል አሰራርን መካተቱን ጠቁመዋል።
በዚህም ከመስከረም 23 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ትግበራው እንደሚጀመር እና በሂደት በተያዘው ዓመት በሁሉም የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ለመተግበር መታቀዱን አብራርተዋል።
በቴክኖሎጂ ትግበራው፣ የቴክኖሎጂ መገልገያ መሳሪያዎች እና መሰረተ ልማቶች ካላቸው ተደራሽነት አንጻር እንዲሁም የቴክኖሎጂ ግንዛቤን ማሳደግ ላይ ተጨማሪ ዝግጅት እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል።
መተግበሪያው የለማው ለፌደራል ፍርድ ቤቶች ቢሆንም ለክልሎችም በሚያገለግል መልኩ በመዘጋጀቱ ክልሎች ወደ ራሳቸው ተጨባጭ ሁኔታ መቀየርና መሰረተ ልማቶችን ዝግጁ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል ሲሉ አስረድተዋል።
በመሳፍንት እያዩ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!