አዲስ አበባ፣ መስከረም 5፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከመስከረም እስከ ኅዳር ባሉት ወራት የወባ በሽታ ስርጭት የሚበዛ በመሆኑ ተጋላጭ አካባቢዎችን በመለየት የመከላከል ሥራ እየተሰራ ይገኛል።
የክልሉ ጤና ቢሮ የወባ መከላከል ፕሮግራም ከፍተኛ ባለሙያ ዶ/ር አንተነህ ካሳዬ ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን እንዳሉት፤ የወባ በሽታን መከላከል እና መቆጣጠር ትኩረት ተሰጥቶታል።
በዚህም ተጋላጭ አካባቢዎችን በመለየት ማህበረሰቡን ያሳተፈ የወባ በሽታ መከላከል እና መቆጣጠር ስራ እየተሰራ ነው ብለዋል።
በክልሉ ከ1 ሚሊየን በላይ የአልጋ አጎበር ለበሽታው ተጋላጭ ለሆኑ አካባቢዎች ማህበረሰብ መሰራጨቱን ተናግረዋል።
በተጨማሪም የበሽታውን ስርጭት ለመከላከል እና ለመቆጣጠር ማህበረሰቡ ግንዛቤ እንዲኖረው እየተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል።
በኢብራሂም ባዲ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!