አዲስ አበባ፣ መስከረም 5፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የቻይናው ቾንግከንግ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹን በሰው መሰል ሮቦቶች እና ውሾች ያደረገው አቀባበል ትኩረትን ስቧል፡፡
በደቡብ ምዕራብ ቻይና የሚገኘው ዩኒቨርሲቲው አዲስ ተማሪዎችን በሰው ሮቦቶች እና ውሾች በመታገዝ አቀባበል ያደረገ ሲሆን÷ ሮቦቶቹ የተማሪዎቹን ሻንጣ በመቀበል የእንኳን ደህና መጣችሁ አቀባበል ከማድረግ በተጨማሪ በመድረክ ላይ የተለያዩ ትዕይንቶችን አቅርበዋል፡፡
የብዙዎችን አድናቆት ያገኘው ለተማሪዎች በሮቦቲክ ሰዎች እና ውሾች የተደረገው አቀባበል በዩኒቨርሲቲው ታሪክም የመጀመሪያው ነው፡፡
ይህም የዩኒቨርሲቲው ብሎም የሀገሪቱ የቴክኖሎጂ ዕድገትን በግልጽ ከማሳየቱም በላይ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ልህቀትን ያመላከተ መሆኑ ነው የተነገረው፡፡
ሮቦቶቹ የተማሪዎቹን ሻንጣ በአግባቡ ወደ ክፍላቸው በማድረስና አዲሱ የዩኒቨርሲቲያቸውን ግቢ በማስጎብኘት የተሰጣቸውን ኃላፊነት በብቃት መወጣቱም ተመላክቷል።
ሮቦቶቹ ተማሪዎቹ የእንግድነት ስሜት እንዳይሰማቸው የቤተሰባዊነት ስሜትን በመላበስ የተሰሩ ናቸው፡፡
በቻይና መሰል የሮቦቶች አቀባበል ከጊዜ ወደ ጊዜ በየዩኒቨርሲቲዎቹ እየተለመደ በመምጣት በዘርፉ ቴክኖሎጂ የደረሰበትን ደረጃ በማሳየት ላይ ይገኛል፡፡
በአቤል ነዋይ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!