የሀገር ውስጥ ዜና

በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የሕዳሴ ግድብ መመረቁን አስመልክቶ የድጋፍ ሰልፎች እየተካሄዱ ነው

By Adimasu Aragawu

September 16, 2025

አዲስ አበባ፣ መስከረም 6፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ መመረቁን አስመልክቶ ‘በኅብረት ችለናል’ በሚል መሪ ሐሳብ ሕዝባዊ የድጋፍ ሰልፎች እየተካሄዱ ነው።

ሰልፉ ባሕር ዳር ከተማን ጨምሮ በጎንደር፣ ደሴ፣ ደብረ ብርሃን፣ ደብረ ማርቆስ፣ ወልዲያ፣ ሰቆጣ፣ ደብረ ታቦር እና በሌሎች ከተሞች ከማለዳው ጀምሮ እየተካሄደ ይገኛል።

በሰልፉ ላይ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተሳተፉ ሲሆን የሕዳሴ ግድብ የብልጽግናችን አሻራ፣ ግድባችን – የመቻል ማሳያ የማንሰራራት ጅማሮ ምልክት፣ የሚደገም ድል፣ የሚጨበጥ ብስራት – ሕዳሴ ግድብ እና ለግድቡ የተባበረ ክንድ ለብልጽግናችን ይተጋል የሚሉ መፈክሮች ተሰምተዋል።

በተጨማሪም ግድባችን በራስ አቅም በአፍሪካዊነት ኩራት የተገነባ እውነት፣ ግድባችን የህብረ ብሔራዊነታችን እና የአንድነታችን መሰረት፣ ግድባችን የመነሳት ደወል ብስራት የኢትዮጵያዊነት ድምቀት የሚሉ እና ሌሎች በግድቡ ግንባታ የተገኙ ድሎችን የሚዘክሩ እና ህብረ ብሔራዊ አንድነትን የሚያጠናክሩ መልዕክቶች ተላልፈዋል።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!