አዲስ አበባ፣ መስከረም 6፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅን ተከትሎ በባሕር ዳር ከተማ ሕዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ ተካሂዷል።
በሰልፉ ላይ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት ሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው ቢዚህ ወቅት÷ ኢትዮጵያ የነጻነት ባለቤት መሆኗን የማይፈልጉ ጠላቶች ሲገፏት እና ሲወጓት መኖራቸውን አንስተው÷ ኢትዮጵያውያን ግን ማሸነፍ ልምዳቸው ነውና ድል ሲያደርጉ ኖረዋል ብለዋል።
ኢትዮጵያን ከደህንነት እና ከግጭት ለማውጣት ሥራ መጀመሩን ገልጸው÷ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የብልጽግና ጅማሮ መሆኑን አንስተዋል።
ሕዳሴ የአሸናፊነት ማሳያ፣ የብልጽግና ጉዞ ማብሰሪያ፣ የአንድነት ማሳያ እንዲሁም በአንድነት ማሳካት የማንችለው እንደሌለ ያሳየ ዳግማዊ ዓድዋ ነው ሲሉም ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ ያሰበችውን እያሳካች ትቀጥላለች፤ የሚያቆማት የለም ያሉት ከንቲባው÷ የባሕር ዳር ከተማ ነዋሪዎች ለሀገር የሚጠበቅባቸውን ለማበርከት ዝግጁ መሆናቸውንም አረጋግጠዋል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!