የሀገር ውስጥ ዜና

ሕዳሴ ግድብ የመቻላችን ልኬት፤ የአንድነታችን ማሕተም ነው – አቶ አወሉ አብዲ

By Yonas Getnet

September 16, 2025

አዲስ አበባ፣ መስከረም 6፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የመቻላችን ልኬት፤ የአንድነታችን ማሕተም ነው አሉ የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አወሉ አብዲ።

የሕዳሴ ግድብ በስኬት ተጠናቅቆ መመረቁን በማስመልከት በአሰላ ከተማ የፓናል ውይይት እየተካሄደ ይገኛል።

በፓናል ውይይቱ ላይ አቶ አወሉ አብዲ እንዳሉት፤ የሕዳሴ ግድብ ከፍፃሜው እንዲደርስ ብዙ መስዋዕትነት ተከፍሏል።

የግንባታ ሂደቱ በውስብስብ ችግሮች ውስጥ ወድቆ እንደነበር አስታውሰው፤ ይህንን በማረም ግድቡ በተሳካ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ ተደርጓል ብለዋል።

ግድቡ የላብ፣ የደም እና የዕምባ ውጤት ያሉት አቶ አወሉ፤ ይህም ትልቅ ትርጉም ያለው የመቻላችን ልኬት፣ የአንድነታችን ማሕተም ነው ሲሉ ተናግረዋል።

ሕዳሴ በአንድነት እና በሕብረት ሁሉም እንደሚቻል ህብረተሰቡ ያሳየበት እንደሆነ ገልጸው፤ ግንባታው ለፍፃሜ እንዲበቃ ሕዝቡ ላደረገው ያልተቆጠበ ድጋፍ አመስግነዋል።

በወንድሙ አዱኛ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!