የሀገር ውስጥ ዜና

የፋና ላምሮት 5ኛው የአሸናፊዎች አሸናፊ የፍፃሜ ውድድር በመጪው ቅዳሜ ይካሄዳል

By Melaku Gedif

September 16, 2025

አዲስ አበባ፣ መስከረም 6፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ከሁለት ወራት በላይ በብርቱ ፉክክር ሲካሄድ የቆየው የፋና ላምሮት 5ኛው የአሸናፊዎች አሸናፊ የፍፃሜ ውድድር በመጪው ቅዳሜ መስከረም 10 ቀን 2018 ዓ.ም ይካሄዳል።

በውድድሩ ለፍጻሜ የበቁት ጴጥሮስ ማስረሻ፣ እየሩሳሌም አሰፋ፣ እዮቤል ፀጋዬ እና ኤፍሬም ጌታቸው ብርቱ ፉክክር ይጠብቃቸዋል።

የዕለት አቀራረብ ላይ መሰረት በማድረግ በዳኞች እና በተመልካቾች ድምፅ የውድድሩ አሸናፊ የሚለይ ሲሆን፤ በውድድሩ አንድ እንግዳ በክብር ዳኛነት ይገኛል።

በ13ኛው ሳምንት አራት ምርጥ ተወዳዳሪዎችን ይዞ የፍፃሜ ውድድሩን የሚያካሂደው ፋና ላምሮት 5ኛው የአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድር ከ3 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር በላይ ሽልማት የተዘጋጀለት ሲሆን፤ የዋንጫ እና የአዲስ ሙዚቃ ሽልማት ያበረክታል።

ይህን ደማቅ ውድድር በቀጥታ ስርጭት በመጪው ቅዳሜ ከ6:00 ጀምሮ በፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ሁሉም የሚዲያ አማራጮች ይከታተሉ።