የሀገር ውስጥ ዜና

መደመር ተብሎ የተጀመረው የሀገራዊ ዕሳቤ ጉዞ የመደመር መንግሥት ላይ ደርሷል – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን

By Melaku Gedif

September 16, 2025

አዲስ አበባ፣ መስከረም 6፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) መደመር ተብሎ የተጀመረው የሀገራዊ ዕሳቤ ጉዞ ዛሬ የመደመር መንግሥት ላይ ደርሷል አሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፡፡

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተጻፈው ‘የመደመር መንግሥት’ የተሰኘው መጽሐፍ በዛሬው ዕለት ተመርቋል፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን በማህበራዊ ትስስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ ÷ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እንኳን ደስ ያለዎት ብለዋል፡፡

መደመር ተብሎ የተጀመረው የሀገራዊ ዕሳቤ ጉዞ ዛሬ የመደመር መንግሥት ላይ ደርሷል ሲሉም ተናግረዋል፡፡

በአንድ በኩል እየመሩ፣ እየሠሩ፤ በሌላ በኩል ደግሞ እያጠኑ፣ እየመረመሩ ‘የመደመር መንግሥት’ መጽሐፍን በማበርከታቸውም ምስጋና አቅርበዋል፡