የሀገር ውስጥ ዜና

የመደመር መንግሥት ያልተሄደበትን መንገድ መጓዝ ይመርጣል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)

By Abiy Getahun

September 17, 2025

አዲስ አበባ፣ መስከረም 7፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የመደመር መንግሥት ያልተሄደበትን መንገድ መጓዝ ይመርጣል አሉ፡፡

በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተጻፈው ‘የመደመር መንግሥት’ የተሰኘው መጽሐፍ በትናንትናው ዕለት ተመርቋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ‘የመደመር መንግሥት’ የተሰኘው መጽሐፍ ታሪክ ሰሪዎች እንጂ ታሪክ ዘካሪ አንሆንም በሚል መልዕክት የተዘጋጀ ነው ብለዋል፡፡

የመደመር መንግሥት ያልተሄደበትን መንገድ መጓዝ ይመርጣል በማለት ገልጸው፤ ይህንን የመደመር መንግሥት ጉዞ ለማሳየት ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ እና ሱዳን በቂ አስተማሪ ምሳሌ ናቸው ብለዋል፡፡

ሱዳን እኛ ስንለወጥ ሰላማዊ ሀገር ነበረች አሁን ግን የተዛባ ጥያቄ ሲነሳ ቀድሞ በልጆቿ የገነባችውን የካርቱም ኢንተርናሽናል ኤርፖርት አፍርሳዋለች ነው ያሉት፡፡

ሱዳኖች የተከተሉት እና የመረጡት መንገድ አፍራሽ በመሆኑ ለችግር መዳረጋቸውን ጠቁመዋል፡፡

እኛ ደግሞ በገንዘብም፣ በሀሳብም፣ በአሰራርም፣ የገዘፈውን ሕዳሴ ከነስብራቱ ተቀብለን ለፍጻሜ ማብቃት ችለናል ሲሉም አብራርተዋል፡፡

ሕዳሴን ስለጨረስን ማን ሰራው የሚለው ነገር እያከራከረ እንደሚገኝ ገልፀው፤ ይህ ጥያቄ የተነሳው ስለጨረስነው ነው በማለት ተናግረዋል፡፡

ግድቡ ኢትዮጵያውያን ተደምረው ያሳኩት ገድል እና ድል መሆኑን ያስረዱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ የመደመር መንግሥት ስኬት ለመሻማት ጊዜ የለውም ብለዋል።

‘የመደመር መንግሥት’ የተሰኘው መጽሐፍ ታሪክ ሰሪዎች እንጂ ታሪክ ዘካሪ አንሆንም በሚል መልዕክት የተዘጋጀ መጽሀፍ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

በወንድማገኝ ጸጋዬ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!