አዲስ አበባ፣ መስከረም 7፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ ከተሞች የተካሄደው የድጋፍ ሰልፍ ከደስታ የተሻገረ በመተባበር የመፈጸም አቅምን የሚያሳይ ነው አሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት÷ ተፈጥሮን እንደ ዐይኑ ብሌን መንከባከብ እና ማልማት ለሚያውቀው የኦሮሚያ ክልል ሕዝብ ሕዳሴ ልዩ ትርጉም አለው ብለዋል።
ውሃ ለኦሮሞ በሕይወቱ፣ በባህሉ፣ በታሪኩ እና በሕዝባዊ እሴቶቹ ሁሉ ትልቅ ቁርኝት ያለው የማንነት ቀለሙ ነው ሲሉም አመልክተዋል።
በታላቁ ወንዝ ዓባይ ላይ ለተገነባው የሕዳሴ ግድብ ዛሬ በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ ከተሞች የተካሄደው የድጋፍ ሰልፍ ከደስታ የተሻገረ በመተባበር የመፈጸም አቅምን የሚያሳይ እንደሆነም ገልጸዋል።
በድጋፍ ሰልፎቹ የተስተጋቡት ድምጾችም ልማትን የመናፈቅ ሰላምን አብዝቶ የመፈለግ፣ በመደመር የኢትዮጵያን የማንሰራራት ዘመንን በብዙ ድሎች የማጽናት ብርቱ መሻቶች እንደሆኑ አይተናልም ነው ያሉት፡፡
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡