አዲስ አበባ፣ መስከረም 7፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የመስቀልና ኢሬቻ በዓላት ማክበሪያ ቦታዎችን ምቹና ንፁህ የማድረግ ስራ እየተሰራ ነው አለ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ።
የአዲስ አበባ እና ሸገር ከተማ አስተዳደር በጋራ በመሆን ከአጎራባች አካባቢዎች ለሚመጡ የበዓሉ ታዳሚዎች የተሻለ አቀባበል ለማድረግ ዝግጅት ማድረጋቸውም ተጠቁሟል።
የኤጄንሲው ዋና ዳይሬክተር ገዛኸኝ ዴሲሳ ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን እንዳሉት÷ የበዓላት የማክበሪያ ቦታዎችን ምቹና ንፁህ የማድረግ ስራ ተጀምሯል።
በዚህም የአዲስ አበባ ከተማ የጤና ቢሮ፣ እሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከል ስራ አመራር ኮሚሽን እንዲሁም የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣንን ጨምሮ ሌሎች ባለድርሻ አካላት የተሳተፉበት ግብረ ኃይል ተቋቁሞ ወደ ስራ ተገብቷል ብለዋል።
ለበዓሉ ታዳሚዎች የተሻለ አቀባበልና መልካም መስተንግዶ ለማድረግ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡
በዓሉ ከተጠናቀቀ በኋላ ቦታዎችን መልሶ በማጽዳት የማስተካከል ስራ የዝግጅቱ አካል ተደርጎ እየተሰራ እንደሚገኝም አስረድተዋል፡፡
በታሪክ አዱኛ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!