አዲስ አበባ፣ መስከረም 7፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል በ2018 በጀት ዓመት ከ20 ሺህ በላይ ይዞታዎችን በካዳስተር ለመመዝገብ እየተሰራ ነው አለ የክልሉ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ።
በቢሮው የካዳስተር ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ ቤተልሔም ተሾመ ለፋና ዲጂታል እንዳሉት÷ የከተማ መሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ አያያዝ ግንዛቤ ከጊዜ ወደ ጊዜ በክልሉ እየጨመረ መጥቷል።
በክልሉ ምሥረታ ወቅት በአምስት ከተሞች ብቻ ተግባራዊ የሆነው የከተማ መሬት ምዝገባ ሥራ አሁን ላይ ወደ 16 ከተሞች ማሳደግ መቻሉን ገልጸው÷ በዚህም ከይዞታ መብት ጋር የሚነሱ የመልካም አስተዳደርና አግልግሎት አሰጣጥ ችግሮችን መቅረፍ እየተቻለ ነው ብለዋል።
የከተሞችን የመሬት መረጃ አያያዝ ሥርዓት ማዘመን መቻሉንና በሂደቱ ከተሞች ከፍተኛ ገቢ እያገኙ እንደሆነ አንስተዋል።
በበጀት ዓመቱ የተያዘውን ዕቅድ ለማሳካት በየከተሞቹ ነባርና ሰነድ ያላቸው ይዞታዎችን የመለየትና መረጃ ማደራጀት፣ ሁለተኛ ደረጃ የመሬት መቆጣጠሪያ ነጥቦችን መትከል እና ከብሄራዊ የመረጃ ቋት ጋር በሳተላይት በማናበብ የማስተሳሰር ስራ መከናወኑን ጠቁመዋል።
በከተሞች የመሬት አስተዳደር ሥርዓት ያልያዘ በመሆኑ ህገወጥነት በመቀነስ ግልጽነትና ተጠያቂነት ባረጋገጠ መልኩ ተደራሽ ለማድረግ ክልሉ ከተቋቋመበት ጊዜ አንስቶ መጠነ ሰፊ ሥራ እየተተገበረ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡
በአድማሱ አራጋው
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!