አዲስ አበባ፣ መስከረም 8፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ ታሪክ ተናጋሪ ብቻ ሳንሆን ታሪክ ሰሪም ሆነናል አሉ፡፡
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወላይታ ሶዶ ከተማ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ መመረቁን አስመልክቶ የድጋፍና የደስታ መግለጫ ሕዝባዊ ሰልፍ ተካሂዷል፡፡
በሰልፉ ላይ የተገኙት አቶ ጥላሁን ከበደ ባስተላለፉት መልዕክት÷ በሕዳሴው ግድብ ላይ የታየውን አንድነት በማጠናከር ሀገራችንን ብሎም ክልላችንን የብልጽግና እና የመቻቻል ተምሳሌት ለማድረግ በትጋት መስራት አለብን ብለዋል፡፡
ታሪክ ተናጋሪ ብቻ ሳንሆን ታሪክ ሰሪም ሆነናል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ÷ ግድቡ በሕብረትና በአንድነት መቻላችንን ያሳየንበት ነው ሲሉም አብራርተዋል፡፡
በሕዝባችን አንድነት የተጠናቀቀው ሕዳሴ ግድብ ለሌሎችም ፕሮጀክቶች የሚያነሳሳ ነው ብለዋል።
“በሕብረት ችለናል” በሚል መሪ ሐሳብ በተካሄደው ሰልፍ የፈረስ ጉግስ፣ ስፖርታዊ ውድድሮች እና ሌሎች መርሐ ግብሮችም ተከናውነዋል፡፡
በመለስ ታደለ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!