የሀገር ውስጥ ዜና

የሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅ የኢትዮጵያን የብልፅግና ስኬት አይቀሬነት ያረጋገጠ ነው

By Yonas Getnet

September 18, 2025

የሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅ የኢትዮጵያን የብልፅግና ስኬት አይቀሬነት ያረጋገጠ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 8፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የታላቁ ኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ መገንባት የኢትዮጵያን የብልፅግና ስኬት አይቀሬነት ያረጋገጠ ነው አሉ በም/ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የዲላ ክላስተር አስተባባሪ መሪሁን ፍቅሩ (ዶ/ር) ።

የታላቁ ኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ መመረቅን በማስመልከት በዲላ ከተማ ሕዝባዊ የድጋፍ እና የደስታ መግለጫ ሰልፍ ተካሂዷል።

መሪሁን ፍቅሩ (ዶ/ር ) በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ የሕዳሴ ግድብ ግንባታ ስኬት የኢትዮጵያ የከፍታና የማንሰራራት ጉዞ ማሳያ ነው።

የታላቁ ሕዳሴ ግድብ መገንባት የመቻል አቅም የታየበት እንደሆነ እና ከድህነት አዙሪት በመውጣት የኢትዮጵያን የብልፅግና ስኬት አይቀሬነት ያረጋገጠ ነው ሲሉም ተናግረዋል።

ደስታው የሁላችንም ነው ያሉት ኃላፊው÷ ለዚህ ስኬት በመብቃታችን እንኳን ደስ አለን ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።

የጌዴኦ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዝናቡ ወልዴ (ዶ/ር) በበኩላቸው÷ ሕዳሴ ግድብ በሕብረት በመቆም፤ በፅናትና በትጋት ለስኬት እንዲበቃ መደረጉን ተናግረዋል።

የዞኑ ሕዝብ ለግድቡ ግንባታ ሁለንተናዊ ድጋፍ ሲያደርግ መቆየቱን አስታውሰው÷ በቀጣይ ግዙፍ ሃገራዊ ፕሮጀክቶች እንዲሳኩ ተሳትፎውን እንዲያጠናክር ጥሪ አቅርበዋል።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation

Facebook FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)

Telegram t.me/fanatelevision

Website www.fanamc.com

TikTok www.tiktok.com/@fana_television

WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29

Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment

Facebook WMCC

TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment

Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!