ቢዝነስ

አየር መንገዱ በአገልግሎት ጥራትና ደንበኛ እርካታ ላይ የማይናወጥ አቋሙን በተግባር እያሳየ ነው – አቶ መስፍን ጣሰው

By Adimasu Aragawu

September 18, 2025

አዲስ አበባ፣ መስከረም 8፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአገልግሎት ጥራት፣ በደንበኛ እርካታ እና በፈጠራ ላይ የማይናወጥ አቋሙን በተግባር እያረጋገጠ ነው አሉ የአየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው።

አየር መንገዱ እ.ኤ.አ በ2026 ለደንበኞች የሚያቀርባቸውን የበረራ ላይ ምግቦች ዝርዝር እና ቅምሻ መርሐ ግብር አከናውኗል።

አቶ መስፍን ጣሰው በዚሁ ወቅት እንዳሉት÷ በአየር ትራንስፖርት ላይ የሚቀርቡ ምግቦች የመንገደኞች ፍላጎትና ምርጫ ያማከሉ ናቸው።

ይህ ልዩ ዝግጅት የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአገልግሎት ጥራት፣ በደንበኛ እርካታ እና በፈጠራ ላይ ያለውን የማይናወጥ ቁርጠኝነት በተግባር እያረጋገጠ መሆኑን ያሳያል ብለዋል።

አየር መንገዱ ዓለም አቀፍ እንደመሆኑ መጠን የደንበኞቹን ፍላጎትና ምርጫ በሟላ መልኩ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን ተናግረው÷ ይህን ማስተናገድ የሚያስችል መሰረተ ልማት በማቋቋም እየሰራ እንደሚገኝ አመልክተዋል።

አየር መንገዱ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነቱን የሚያስቀጥሉ የተሳለጡ አገልግሎቶች መስጠቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ማረጋገጣቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በበረራ ወቅት በምግብ አቅርቦት፣ ለምግብ ደህንነት እና ለአካባቢ አስተዳደር ስርዓቶች የተለያዩ ማረጋገጫዎች እንደተሰጡትም ጠቁመዋል።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!