አዲስ አበባ፣ መስከረም 8፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) አፋር የልማት ጮራ እየፈነጠቀበት ያለ የልማት አርበኞች ምድር ነው አሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፡፡
ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅን በማስመልከት በአፋር ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ሕዝባዊ የድጋፍና የደስታ መግለጫ ሰልፎች ተካሂደዋል፡፡
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በክልሉ የተካሄዱትን ሰልፎች አስመልክተው በማኅበራዊ የትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፥ የኢትዮጵያ ምድረ ቀደምትነት የምስክር ማህተም በሆነው አፋር ዛሬም የኢትዮጵያ ሰንደቅ በድል ሰልፍ ከፍ ብሎ ውሏል ብለዋል።
የአፋር መሬቱም ሰውም ለሀገር ሉዓላዊነት ዋጋ የከፈለ ጀግና ሆኖ ብቻ ሳይሆን የልማት ጮራ እየፈነጠቀበት ያለ የልማት አርበኞች ምድር መሆኑን አውስተዋል።
የታላቁ ሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅ ለኢትዮጵያ ልማት ለሚተጋው ለአፋር ሕዝብ ተጨማሪ ሃብት እና ወኔ ይሆነዋልም ነው ያሉት።
የአፋር ሕዝብ ለልማትና ለሰላም የወገነና የኢትዮጵያን ብሩህ ዘመን ዕውን ለማድረግ ያለመ መሆኑን በድጋፍ ሰልፉ ላይ በተስተጋባው ድምጽ ተረድነተናል ብለዋል፡፡