የሀገር ውስጥ ዜና

የ2018 ዓ.ም የኢሬቻ በዓል የፊታችን መስከረም 24 እና 25 ቀን ይከበራል

By Yonas Getnet

September 18, 2025

አዲስ አበባ፣ መስከረም 8፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የዘንድሮው የኢሬቻ በዓል መስከረም 24 ቀን በሆረ ፊንፊኔ እና መስከረም 25 ቀን 2018 ዓ.ም በሆረ ሀርሰዲ ይከበራል፡፡

የኦሮሞ አባገዳዎች ኅብረት በሰጡት መግለጫ ÷ የኢሬቻ በዓል የምሥጋና፣ የአንድነት፣ የፍቅር እና የእርቅ በዓል መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

ስለሆነም ማሕበረሰቡ የኢሬቻ በዓልን ሲያከበር የኦሮሞ ባሕል እና እሴትን በጠበቀ መልኩ መሆን እንዳለበት አንስተዋል፡፡

የዘንድሮው የኢሬቻ በዓልም መስከረም 24 ቀን በሆረ ፊንፊኔ እና መስከረም 25 ቀን 2018 ዓ.ም ደግሞ በሆረ ሀርሰዲ እንደሚከበር አመልክተዋል፡፡

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!