አዲስ አበባ፣ መስከረም 8፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) አሰልጣኝ ጆዜ ሞሪኒሆ የፖርቹጋሉ ክለብ ቤኔፊካ አሰልጣኝ መሆናቸው ይፋ ሆነ።
ፖርቹጋላዊው አሰልጣኝ በቤኔፊካ እስከ ፈረንጆቹ 2027 የሚያቆያቸውን የሁለት ዓመት ኮንትራት ተፈራርመዋል።
ሞሪኒሆ ከዚህ ቀደም ሪያል ማድሪድ፣ ኢንተር ሚላን፣ ቼልሲ፣ ቶተንሃም ሆትስፐር እንዲሁም ፖርቶን የመሳሰሉ ክለቦችን ማሰልጠናቸው የሚታወስ ነው።
በቅርቡ ከቱርኩ ክለብ ፌነርባቼ የተሰናበቱት አሰልጣኝ ጆዜ ሞሪንሆ ወደ ኃላፊነት በመመለስ የቤኔፊካ አሰልጣኝ ሆነዋል።
አሰልጣኙ በዚህ የውድድር ዓመት በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ቤኔፊካን እየመሩ የቀድሞ ክለቦቻቸውን ቼልሲ እና ሪያል ማድሪድ የሚገጥሙ ይሆናል።
በወንድማገኝ ፀጋዬ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!