ጤና

የወባ መከላከያ ክትባት በሽታውን ለማጥፋት…

By Adimasu Aragawu

September 18, 2025

አዲስ አበባ፣ መስከረም 8፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የወባ መከላከያ ክትባት በሽታውን ለማጥፋት በማለም ለተጀመረው ርብርብ ትልቅ እገዛ ያደርጋል አሉ የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጄ ዱጉማ።

ዶ/ር ደረጄ የወባ መከላከያ ክትባትና የአልጋ አጎበር ስርጭትን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በደቡብ ኦሞ ዞን ቱርሚ ከተማ በመገኘት በይፋ አስጀምረዋል።

በወቅቱም በሽታን በ2030 ለማጥፋት እየተደረገ ባለው ርብርብ የጸረ ወባ ክትባት ዘመቻው ከፍተኛ እገዛ እንዳለው ገልጸው÷ ክትባቱ የወባ ስርጭት ባለባቸው 58 ወረዳዎች እንደሚካሄድ አመልክተዋል።

ክትባቱ በዓለም ጤና ድርጅት ውጤታማነቱ የተረጋገጠና አስተማማኝ መሆኑን አንስተው፥ ወላጆችና አሳዳጊዎች ከ5 ዓመት በታች የሆኑ ህፃናትን በማስከተብ ግዴታቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል።

ከዚህ በተጓዳኝ ከ3 ነጥብ 5 ሚሊየን በላይ የአልጋ አጎበሮች የወባ ጫና ላሉባቸው አካባቢዎች እንደሚሰራጩ መናገራቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!